ቢሮ ለ1884 መምህራን የማስተማር ስነ-ዘዴ /PGDT/ ስልጠና በክረምት መርሀ ግብር ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስራ ውል ስምምነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ተፈራረመ፡፡
(ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ1884 መምህራን የPGDT/የማስተማር ስነ-ዘዴ/ ስልጠና በክረምት መርሀ ግብር ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስራ ውል ስምምነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ተፈራርሟል፡፡
በፊርማ መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ያደረገው የጋራ ስራ ውል ስምምነት ለ1884 መምህራን በክረምት በርሀ ግብር የPGDT ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማረገገጥ እና የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማጎልበት ትልቅ ሚና እንዳለው የጠቀሱት ሀላፊው ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በሚያወጣው የስልጠና መስጫ መርሀ ግብር መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ቢሮ ያመቻቸዉን ይህንን የ PGDT ስልጠና እድል መምህራን በመጠቀም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሚናቸዉን ሊወጡ ይገባል ያሉት ሀላፊው ስምምነቱ በ2019 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰጠው ትምህርት የቅድመ ዝግጅት ስራ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር የቆየሰው ደሴ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠዉን ትምህርት ስኬታማና ጥራቱ የተረጋገጠ እንዲሆን እየሰራቸዉ የሚገኙ ስራዎች አስደሳች መሆናቸውን ጠቅሰው በክረምት መርሀ ግብር ላይ የሚሰጠው የ PGDT ስልጠና ስኬታማ እንዲሆን በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
.