Announcement የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢሬቻ በአልን አስመልክቶ የፓናል ውይይት አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢሬቻ በአልን አስመልክቶ የፓናል ውይይት አካሄደ።

03rd October, 2025

የፓናል ውይይቱ "ኢሬቻ ለሃገር ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል በሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ አጠቃላይ ሰራተኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ታላቅ አክብሮት ከሚሰጣቸው በአላት አንዱ የሆነ የማንነት መገለጫ የአንድነትና የአብሮነት መሰላል ነው ሲሉ ተናግረዋል::

የኢሬቻ በአል ከኦሮሞ ህዝብ ባሻገር ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚያከብሩት በአል መሆኑን የተናገሩት ቢሮ ኃላፊው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮም የዘንድሮው በአል እሴቶቹን ጠብቆ እንዲከበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ የሚመጡ እንግዶችን ከመቀበል ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ  እንደሚገኝ በመግለጽ የዛሬው ፓናል ውይይት ከኢሬቻ በአል አከባበር ጋርም ሆነ ከገዳ ስርአት ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑን አመላክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው የኢሬቻ በአል አንድነትን እና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር በአል እንደመሆኑ የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በአል እሴቱን ጠብቆ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የቢሮው ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪው ዶክተር ቁልቁሉ ስለ ኢሬቻ በአል አከባበር እና የገዳ ስርአትን በተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

.

Copyright © All rights reserved.