Announcement የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የ90 ቀን ተግባራት አካል የሆነውን የክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄደ።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የ90 ቀን ተግባራት አካል የሆነውን የክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄደ።

09th August, 2025

በእለቱ የትምህርት  አመራሮች ፣መምህራን ፣ባለሙያዎችና ተማሪዎች   በስፍራው በመገኘት በበጎ ፈቃደኝነት  ደም ለግሰዋል። 

በደም ልገሳ   መርሃግብሩ ላይ  የክፍለ  ከተማው ትምህርት  ፅ/ቤት ኃላፊ  ወ/ሮ ለሊስቱ ተስፋዬ ተገኝተው  ራሳቸው ደም በመለገስ ፕሮግራሙን ያስጀመሩ ሲሆን የክረምት  በጎ ፈቃድ  ስራ አካል በሆነው  የደም  ልገሳ ተግባር   የትምህርት  ማህበረሰቡን  በማስተባበር የደም  ልገሳ ሂደቱ በየትምህርት  ቤቶች  ተጠናክሮ የቀጠለ  መሆኑን  በመግለፅ መምህራን  ከትውልድ  ቀረፃ ስራዎች  ባሻገር  በበጎ  ፈቃድ  ስራዎች  ላይ  በመሳተፍ  የደም መለገስ  ተግባር  እያከናወኑ  እንደሚገኙና ወደፊትም  በትኩረት  እንደሚሰራ ተናግረዋል ። 

ደም ሲለግሱ ያገኛነቸው በበጎ ፈቃደኞች በበኩላቸው ደም መለገስ ለሰዎች ህይዎትን መለገስ እንደሆነ በመግለጽ በደም እጦት  ምክንያት  የሰው ህይወት  እንዳይልፍ  ደም መለገስ የሚችል ሰው በሙሉ በበጎ   በፈቃደኝነት  ደም በመለገስ የሰዎችን  ህይወት መታደግ  እንዳለባቸው  አስገንዘበዋል ።


.

Copyright © All rights reserved.