About የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተቋሙን የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሞ አፀደቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተቋሙን የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሞ አፀደቀ።

05th April, 2025

(መጋቢት 24/2017 ዓ.ም) በመርሀግብሩ የቢሮው የእቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የተቋሙን የ9 ወር ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመልካም አስተዳደር እና የቅንጅታዊ ስራዎችን ሪፖርት አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የቢሮው የስትራቴጂክ ካውንስል እና ጠቅላላ ካውንስል አባላት የተቋሙን የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መገምገማቸውን ጠቁመው በሪፖርቱ ዙሪያ ከቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚሰጡ ሀሳቦችን በማካተት እና ሪፖርቱን በማጽደቅ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚላክ አመላክተዋል። የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀሙ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።

የቢሮው ባለሙያዎች በቀረቡት ሪፖርቶች መነሻ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው በቢሮ አመራሮች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የቢሮ ባለሙያዎች በቀሪ የትግበራ ምዕራፍ የተሻለ ስራ በመስራት ተቋሙ በአመቱ መጨረሻ ውጤታማ እንዲሆን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮች አስገንዝበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.