በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በተመረጡ ክላስተር ማዕከላት ከሐምሌ 6 ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር ተገለፀ።
(ሀምሌ 4/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ለተመረጡ ቶፕ 30 የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በክረምት መርሐ ግብር ማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት በቂ ዝግጅት በማድረግ ሰኞ ሐምሌ 6 በተመረጡ የክላስተር ማዕከላት ትምህርቱ መሰጠት ይጀምራል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርቱ እንደሚሰጥ ገልፀው ፤ ትምህርቱ በሳምንት 5ቀን ለክረምት ወቅት ብቻ በተዘጋጀ ኮንደንስድ ካሪኩለም እንደሚሰጥ ገልፀው በማስተማሪያ ስነዘዴው x ን የማረም ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረግ ተማሪዎች ስህተቶቻቸውን እያረሙ በርካታ ጥያቄዎች የሚሰሩበት እንዲሁም ትርፍ ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያውሉ የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል::
ዶክተር ዘላለም በመርሃ ግብሩ 51,523 ተማሪዎችና 1,800 መምህራን ትምህርቱን ለመስጠት ምዝገባ ማካሄዳቸውን ገልፀው በመርሀ ግብሩ የሚሳተፉ የመንግስት እና የግል ተማሪዎች በተገለፀው ቀን በተመረጡ 63 ክላስተር ማዕከላት በመገኘት ትምህርቱን እንዲከታተሉና ስራው በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ተማሪዎችና መምህራን ትምህርቱን ሲያጠናቅቁ የእውቅና ሰርተፍኬት እንደሚሰጣቸው የገለፁ ሲሆን ተማሪዎች በዋናነት ለሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል::
.