About የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ4ኛ ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ላይ ውይይት አካሄደ።

የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ4ኛ ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ላይ ውይይት አካሄደ።

14th June, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም በክፍለ ከተማና ትምህርት ቤቶች የ4ኛ ሩብ አመት የምገባና ግብዓት እቅድ አፈጻጸም ላይ ድጋፍና ክትትል ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በድጋፍና ክትትል ግብረ መልሱ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

የቢሮው የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ብርሃነመስቀል በድጋፍና ክትትሉ የሚገኙ ውጤት መሰረት ቢሮው የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ  ፍረጃ የሰጠ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የተሻለ የሰሩትን ለማበረታታት እውቅና የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል :: አክለውም በግብረ መልሱ መሰረት እጥረት ያለባቸውን ደግሞ በቀጣይ ጊዜ የተሻለ ለመስራት ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል ::

የምገባ ቁጥጥር ቡድን መሪ  የሆኑት አቶ ናትናኤል ገብረዋህድ የድጋፍና ክትትል ግብረመልሱን ውጤት ያቀረቡ ሲሆን በ11ዱ ክፍለ ከተሞች የትምህርት ቤት መሻሻል ርዕሰ መምህራን እና ቡድን መሪዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ባለሙዎች ተሳትፈዋል።

.

Copyright © All rights reserved.