ድጋፍና ክትትሉ የስራክፍሎቹን የ2017 በጀት አመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የሪፎርም ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፤የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የቁልፍ ሥራዎች አመላካች (KPI) ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ መካሄዱን ከቢሮው የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበጀት አመቱ አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ የቁልፍ ሥራዎች አመላካች ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በተደጋጋሚ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ጠቁመው ድጋፍና ክትትሉ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት የነበሩ አፈጻጸሞችን መነሻ በማድረግ በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ከሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ ጋር በመሆን የምዘና ሂደቱን በተከታተሉበት ወቅት አስታውቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ በበኩላቸው በትላንትናው እለት ተመሳሳይ ድጋፍና ክትትል በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈትቤቶች መካሄዱን ገልጸው በቀጣይ ከቢሮ ጀምሮ አስከ ትምህርት ቤት ድረስ የበጀት አመቱን አፈጻጸም መሰረት ያደረገ ምዘና የሚካሔድ መሆኑን አመላክተዋል፡፡