የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 ትምህርት ዘመን 4ኛ ሩብ ዓመት የሪፎርም ፣ አገልግሎት አሰጣጥና ቁልፍ ሥራዎች አመላካች (KPI) ሥራዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ፅ/ቤቶች ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ይገኛል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ በየካ ክፍለ ከተማ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች ባሉ ትምህርት ፅ/ቤቶች በመገኘት ድጋፍና ክትትሉ እየተካሄደ ያለበትን ሁኔታ ተመልክተዋል:: በምልከታቸው ድጋፍና ክትትሉ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ ተናግረው ድጋፍና ክትትሉ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ከመገባቱ በፊት ማሻሻያ ማድረግ የሚገቡ ሥራዎች ላይ በትኩረት ለመስራት ያስችላል ብለዋል::
የድጋፍና ክትትል ስራው ሐምሌ 3 እና 4 በ11ዱ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ፅ/ቤቶችና በቢሮ ዳይሬክቶሬቶች እንደሚካሄድ መገለፁ የሚታወቅ ሲሆን በነገው እለት ለቢሮ ዳይሬክቶሬቶች እንሚካሄድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል::