About በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙት 3ቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙት 3ቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።

14th June, 2025

የጥያቄና መልስ ውድድሩ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች፣በገላን የወንዶች እንዲሁም በብርሀን የአይነስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ነው የተካሄደው።

በጥያቄና መልስ ውድድሩ ቀደም ሲል በሶስቱም ትምህርት ቤቶች በተካሄደ ተመሳሳይ ውድድር አሸናፊ የሆኑ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን መርሀግብሩ ተማሪዎቹ በክፍል ውስጥ የተማሩትን ትምህርት በማስታወስ ለብሔራዊ ፈተና በአግባቡ እንዲዘጋጁ የሚያስችል መሆኑን የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ሱፐር  ቫይዘር የሆኑት አቶ ጸጋዬ አሰፋ አስታውቀዋል።

ሱፐር ቫይዘሩ አያይዘውም በአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር በየአመቱ ሳይቆራረጥ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዘንድሮው ውድድ አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች ዕውቅና መሰጠቱን አመላክተዋል።

በዛሬው ውድድር በማህበራዊ ሳይንስ 1ኛ.ተማሪ መቅደላዊት ዮሴፍ ከእቴጌ መነን  2ኛ.ተማሪ አብዱረህማን አደም እና ተማሪ አበባየሁ አሰፋ ከብርሀን የአይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት አሸንፈዋል።

በተፈጥሮ ሳይንስ  1ኛ.ተማሪ ዳዊት ፈይሳ ከገላን 2ኛ.ተማሪ ናኦል እጅጉ ከገላን እንዲሁም 3ኛ ተማሪ ደጀኔ በለጠ በተመሳሳይ ከገላን አሸናፊ ሆነዋል።

በትምህርት ቤት ደረጃ በማህበራዊ ሳይንስ ብርሀን የአይነ ስውራን አዳሪ እንዲሁም በተፈጥሮ ሳይንስ በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት አሸናፊ ሆነዋል።


.

Copyright © All rights reserved.