የትምህርት ጥራትና የተደራሽነትን ለማጎልበት ታስበው የተገነቡት የትምህርት ዘርፍ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ዛሬ በይፋ ተመርቀዋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገንብተው ዛሬ ከተመረቁት በአጠቃላይ 8 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ለነዋሪውና ለአገልገግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰጡ እነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል በትምህርት ዘርፉ ላይ ያተኮሩት 3ቱ ግንባታዎች የትምህርት መሠረተ ልማት የሚያሻሽሉ ናቸው።
በምረቃ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ምስክር ነጋሽ እንዲሁም በትምህርት ዘርፉ በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና አመራሮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።
ከዛሬ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ከሆኑት ፕሮጀክቶች መካከል አንድ በክፍለ ከተማው በወረዳ 09 አካባቢ የሚገኘው የብሔራዊ ቅድመ አንደኛ ደረጃ የG+2 ግንባታ ነው። ይህ ፕሮጀክት ከግንቦት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ287 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሲከናወን የቆየ ነው።
ህንፃው በዛሬው እለት ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱ በክፍለ ከተማው የነበረውን የኬጂ መማሪያ፣ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ማዕከል እና የአስተዳደር ቢሮዎች እጥረት ችግር ሙሉ በሙሉ የሚቀርፍ ሲሆን፣ የትምህርት ቤቱን የተማሪዎች የመቀበል አቅምም በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል።