Announcement በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2019 የትምህርት አመት በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2019 የትምህርት አመት በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ።

08th October, 2026

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2019 የትምህርት አመት በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ።


(መስከረም 27/2019 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደረ ለ2019 የትምህርት ዘመን ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ ግንባታቸው ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ ከሆኑ ተቋማት መካከል ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 የሚገኘው ቱሉ ኢጄርሳ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዱ ነው።

በትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎችን፣ቤተ ሙከራ፣ቤተ መጽሐፍትን እንዲሁም የአይ ሲቲ ክፍልን ያካተቱ 2ባለ አራት ወለል ህንጻዎችን ጨምሮ ለአስተዳደር ስራዎችን የሚያገለግል 1 ባለ ሁለት ወለል ሁለገብ ህንጻ እንዲሁም የመመገቢያ አዳራሽና ደረጃቸውን የጠበቁ የመጸዳጃ ቤቶችን አካቶ በከፍተኛ በጀት ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪ ኢንጅነር ሙሉነህ ተክለብርሀን አስታውቀዋል ።

በድን መሪው አያይዘውን በትምህርት ቤቱ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ባለ ሁለት ወለል ህንጻና የመመገቢያ አዳራሽ ግንባታ ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራ ዝግጁ መደረጉን ጠቁመው ከህንጻዎቹ ባሻገር የአጥር እና ምድረ ግቢውን የማስዋብ ስራ መከናወኑን አመላክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.