Announcement የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን 13 ትምህርት ቤቶችን ወደ ደረጃ 4 ለማስገባት በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን አስታወቀ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን 13 ትምህርት ቤቶችን ወደ ደረጃ 4 ለማስገባት በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን አስታወቀ።

30th October, 2026

የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን 13 ትምህርት ቤቶችን ወደ ደረጃ 4 ለማስገባት በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን አስታወቀ።
(ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም) ጽህፈት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች በተገኙበት በ2018 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ውጤታማ ሆነው ደረጃ 4 ከገቡ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው ቦሌ ገርጂ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጥ መርሀግብር አካሂዷል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስራዎች አስተባባሪና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ወይዘሮ መዓዛ ተስፉ በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት በግብአት ፣ በሂደትና ውጤትን መሰረት በማድረግ በተካሄደ ኢንስፔክሽን ደረጃ 4 ከገቡ አራት ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው ቦሌ ገርጂ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጤታማ የሆነበትን አሰራር ሌሎች ተቋማት ተግባራዊ አድርገው በ2019 ዓ.ም ደረጃ 4 ገብተው የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እንዲችሉ ታስቦ የልምድ ልውውጥ መርሀግብሩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ወይዘሮ መዓዛ አያይዘውም በክፍለ ከተማው በ2019 ዓ.ም 9 የቅድመ አንደኛ ፣2 አንደኛ ደረጃ እና 2 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በጥቅሉ 13 ተቋማትን ወደ ደረጃ 4 ለማስገባት ጽህፈት ቤቱ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን ጠቁመው በልምድ ልውውጡ የተሳተፉ ተቋማት ደረጃ 4 የገቡ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ያደረጉትን አሰራር መሰረት በማድረግ በግብአት ፣ሂደትና ውጤት የተሻለ ስራ ሰርተው ደረጃቸውን ማሻሻል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

በመርሀግብሩ ከቦሌ ገርጂ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባሻገር በ2018 ዓ.ም ደረጃ 4 የገቡት ቦሌ 2ኛ ደረጃ እና ለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ በርዕሳነ መምህራን አማካይነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

.

Copyright © All rights reserved.