Announcement የ2019 ዓ.ም የትምህርት አመት ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት የተማሪዎችን ደንብ ልብስ ለስርጭት ዝግጅ መሆን እንደሚገባው ተገለጸ።

የ2019 ዓ.ም የትምህርት አመት ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት የተማሪዎችን ደንብ ልብስ ለስርጭት ዝግጅ መሆን እንደሚገባው ተገለጸ።

13th July, 2026


(ሀምሌ 4/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2019 የትምህርት አመት የተማሪዎችን ደንብ ልብስ ጨምሮ የመምህራንን ጋወን እና የመጋቢ እናቶችን ደንብ ልብስ ለማቅረብ ጨረታ ካሸነፉ የጋርመንት ድርጅቶች እና ከጥራት ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ጋት በጋራ በመሆን በድርጅቶቹ በተካሄደ የ2ኛ ዙር የመስክ ምልከታ ሪፖርት ዙሪያ ውይይት አካሄደ።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በየአመቱ የተማሪዎችን ዩኒፎርም ጨምሮ የመምህራንን ጋወን እና የመጋቢ እናቶችን ደንብ ልብስ በማቅረብ ላይ መሆኑን አስታውሰው ለ2019 የትምህርት አመት የደንብ ልብሶቹን እንዲያቀርቡ የተለያዩ ድርጅቶች በቀረበው ስፔክ መሰረት ጨረታ አሸንፈው ወደ ማምረት ስራ እንዲገቡ መደረጉን አስታውቀዋል።


ኃላፊው አያይዘውም ተማሪዎች ለ2019 የትምህርት አመት በሚመዘገቡበት ወቅት ዩኒፎርምን ጨምሮ ደብተርና መጽሐፍ ስርጭት ስለሚካሄድ የደንብ ልብሶቹን በማምረት ላይ የሚገኙ ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት ገቢ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በበኩላቸው 14 ድርጅቶች ለ2019 የትምህርት አመት የተማሪዎችን እና የመጋቢ እናቶችን ደንብ ልብስና የመምህራንን ጋወን ለማቅረብ ጨረታ በማሸነፍ ውል ፈጽመው ወደ ማምረት መግባታቸውን ተከትሎ በድርጅቶቹ ሁለት ዙር ምልከታ መካሄዱን አስታውሰው ቢሮው በቀጣይ ድርጅቶቹ በቀራቸው ጥቂት ቀናት የደንብ ልብሶቹን በየትምህርት ተቋማቱ ገቢ ማድረጋቸውን ከጥራት ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ጋር በጋራ በመሆን ክትትልና ቁጥጥር የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.