Announcement የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ2018 አጠቃላይ የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ2018 አጠቃላይ የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

26th July, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪ ቅበላን መነሻ በማድረግ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመንግስት ሙሉ ድጎማ የሚቀርቡ የተማሪ ደንብ ልብስ ፤ የመምህራን ገዋን እና የመጋቢ እናቶች ሽርጥ የምርት ሂደትና ስርጭትን በተመለከተ ቢሮው ካዋቀረው የጥራት ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ብርሃነመስቀል በ2018 ዓ.ም የተማሪ ደንብ ልብስ ፤ የመምህራን ገዋን እና የመጋቢ እናቶች ሽርጥ የምርት ሂደትና ስርጭትን በተመለከተ ቢሮው ካዋቀረው የጥራት ኮሚቴ ጋር ውይይት መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች የትምህርት ግብአቶቹን ዝግጅት ቀደም ብለው አጠናቀው ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ስርጭት እንዲካሄድና ከትምህርት ካላንደሩ መጀመሪያ ቀን በፊት ተማሪዎች አስፈላጊ ግብአቶችን አሟልተው ራሳቸውን ለትምህርት እንዲያዘጋጁ ቅድመዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

የምርት ጥራትና ስርጭት ኮሚቴው የተማሪዎች ደንብ ልብስ አቅራቢዎች በተፈለገው ወቅት የግብአት አቅርቦት ለማከናወን ርብርብ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸው ቢሮው ባስቀመጠው ቀነገደብ ርክክብ እንደሚያደርግ አብራርተዋል፡፡

በውይይቱ የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎችና ከቢሮውና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ የጥራት ቁጥጥር ኮሚቴዎች ተሳትፈዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.