Announcement ለ2018 የትምህርት ዘመን የመማርያ ደብተሮች ስርጭት በመከናወን ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ለ2018 የትምህርት ዘመን የመማርያ ደብተሮች ስርጭት በመከናወን ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡

09th August, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች መማሪያ የሚውሉ የመማሪያ ደብትሮች ስርጭት እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በ90 ቀናት ውስጥ ታቅደው እየተከናወኑ ከሚገኙ ተግባራት መካከል ለ2018 የትምህርት ዘመን አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመማሪያና ማስተማሪያ ግብዓቶች ስርጭት አንድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም የመማሪያ ደብተሩ ስርጭት ቀደም ሲል ለክፍለ ከተማዎች 60% መሰጠቱን ጠቅሰው ቀሪ 40% መማሪያ ደብተሮች በመሰራጨት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ከዚህ ቀደም ከደንብ ልብሶች ስርጭት ጋር ተያይዞ ይነሳ የነበረዉን በወቅቱ ይድረስልን ጥያቄ በ90 ቀናት እቅድ ውስጥ ተካቶ በመሰራቱ በ21 ጋርመንቶች የተመረቱ የደንብ ልብሶች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በየትምህርት ቤቶቹ በመሰራጨት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ብርሃነመስቀል በ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪ ደንብ ልብስና የመማሪያ ደብተር ስርጭት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ይህም ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡  

.

Copyright © All rights reserved.