Announcement በከተማ አስተዳደሩ በ2018 የትምህርት ዘመን የተሰጡት የ6ኛና የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተናዎች በስኬት ተጠናቀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በ2018 የትምህርት ዘመን የተሰጡት የ6ኛና የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተናዎች በስኬት ተጠናቀዋል።

20th June, 2026



(ሰኔ 12/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ድረስ የተሰጡት የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ199 የፈተና ጣቢያዎች ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንዲሁም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ201 የፈተና ጣቢያዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጡ ቆይተው በስኬት ተጠናቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክብር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በከተማ አስተዳደሩ ሲሰጡ የቆዩት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተናዎች በስኬት መጠናቀቃቸዉን ገልጸው ለስራዉ ውጤታማነት ከቅድመ ዝግጅት ተግባራት ጀምሮ በየደረጃው የተዋቀሩት የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት አባላት ፣ የፈተና አስፈጻሚዎች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ፣ ወላጆችና ተማሪዎች ሳበረክቱት ለቆዩት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡


ቢሮ ሀላፊው በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን 85,017 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ጠቁመው በፈተናው ሂደት ውስጥ 199 የፈተና ጣቢያ ሀላፊዎች ፣ 767 አስፈታኝ ት/ቤቶች ፣ 782 ሱፐርቫይዘሮች እና 2414 ፈታኞች መሳተፋቸውን አመላክተዋል።


በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናም 86,783 ተማሪዎች ፈተናዉን መውሰዳቸዉን ፤ በፈተናዉ ሂደት ውስጥም 201 ጣቢያ ሀላፊዎች ፣ 667 አስፈታኝ ት/ቤቶች ፣ 793 ሱፐርቫይዘሮች እና 2434 ፈታኞች መሳተፋቸውን ገልጸዋል።


ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራቱ ፈተናው በሁሉም የፈተና መስጫ ጣቢያዎች ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማስቻሉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.