Announcement ቢሮው ከተማ አቀፉ የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራቱን አስታወቀ።

ቢሮው ከተማ አቀፉ የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራቱን አስታወቀ።

13th June, 2026



(ሰኔ 5/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከተማ አቀፉን የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደትን ለመከታተል ወደ ፈተና ጣቢያ ለሚሄዱ የቢሮው ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አበራ በመርሀግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው ከተማ አቀፉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው የፈተና ሂደቱን ለመከታተል በየፈተና ጣቢያው የተመደቡ የቢሮ ባለሙያዎች ፈተናው ያለምንም እንከን ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ 85,004 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በ99 የፈተና ጣቢያዎች እንዲሁም 86,786 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በ201 የፈተና ጣቢያዎች የ2018 ዓ.ም ፈተና ለመፈተን ኦን ላይን መመዝገባቸውን ገልጸው በየፈተና ጣቢያው የተመደቡ የቢሮ ባለሙያዎች ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር በጋራ በመሆን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

.

Copyright © All rights reserved.