Announcement የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በስኬት ተጠናቋል።

የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በስኬት ተጠናቋል።

20th June, 2026



(ሰኔ 10/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም ድረስ የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ199 የፈተና ጣቢያዎች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲስጥ ቆይቶ በዛሬው እለት ተጠናቋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክብር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቅድመ ዝግጅት ተግባራት ጀምሮ ከተማ አቀፍ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የተዋቀሩት የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት አባላት ፣ የፈተና አስፈጻሚዎች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ፣ ወላጆችና ተማሪዎች ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ለነበራቸው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።


ቢሮ ሀላፊው በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 85,017 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ጠቁመው በፈተናው ሂደት ውስጥ 199 የፈተና ጣቢያ ሀላፊዎች ፣ 767 አስፈታኝ ት/ቤቶች ፣ 782 ሱፐርቫይዘሮች እና 2414 ፈታኞች መሳተፋቸውን አመላክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.