Announcement በ2018 ትምህርት ዘመን ትራንስፎርም የሚያደርጉ 129 ትምህርት ቤቶች ላይ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡

በ2018 ትምህርት ዘመን ትራንስፎርም የሚያደርጉ 129 ትምህርት ቤቶች ላይ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡

30th August, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት በ2018 ትምህርት ዘመን ትራንስፎርም የሚያደርጉ 129 ትምህርት ቤቶች ላይ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ የቢሮ ባለሙያዎችና የክፍለከተማ ቡድን መሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡

የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በኦረንቴሽኑ ላይ እንዳሉት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን በየበጀት አመቱ ትራንስፎርም ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ መሆኑን አስታውሰው በቀሪ129 ትምህርት ቤቶች ላ ያሉ የግብአትና መሰረተ ልማቶችን በዚህ ዘመን ለማሟላት እንዲቻል ትምህርት ቤቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም የሚስችል ቼክሊስት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ምከትል ቢሮ ሃላፊው እንዳሉት በድጋፍና ክትትል በሚገኘው ውጤት መሰረት ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠርና ትምህርት ቤቶቹን በግብአት ለማሟላት ቢሮው ቅድመ ዝግጅት እንደሚያደርግ አብራርተዋል፡፡ የአክለውም ድጋፍና ክትትሉን የሚያደርጉ ባለሙያዎች በቼክሊስቱ መሰረት ያለውን ክፍተት ለመለየት የሚያስችል ተአማኒ መረጃ በመሰብሰብ በቀጣይ ለትምህርት ቤቶቹ ለሚደረግ ድጋፍ ግብአት የሚሆን መረጃ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡ 

የዘርፈብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው የድጋፍና ክትትል ቼክሊስቱ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል አያይዘውም የሚገኘው ውጤት የተሻለ የትምህርት ስርዓትን ለማስፈን  ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በድጋፍና ክትትል ስራው የቢሮ ባለሙያዎችና የክፍለከተማ ቡድን መሪዎች እንደሚሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.