የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሚለማመዱባቸው አድራሻዎች ይፋ አድርጋል።
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ ይችላሉ ተብላል።
ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የሚሰጥ መሆኑን ፈተናዎች አገልግሎት ገልፃል። ስለሆነም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኞቹ እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥሪ አቅርባል።