Announcement በ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

በ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

18th October, 2025

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የ2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ቢሮው ቀደም ሲል ሪፖርቱን በማኔጅመንት እንዲሁም በአጠቃላይ ካውንስል አባላት እና የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት መገምገሙን ገልጸው በትምህርት ሴክተሩ በዝግጅት ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራት በተግባር ምዕራፍ የሚከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መሰረት የሚጥሉ በመሆናቸው ክፍለከተሞች በሩብ አመቱ የነበራቸውን አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ የ2018 ዓ.ም የተማሪ ምዝገባ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.