Announcement በትምህርት ተቋማት የ2017ዓ.ም አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ምዘና ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

በትምህርት ተቋማት የ2017ዓ.ም አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ምዘና ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

02nd August, 2025

ምዘናው የተቋማቱን የ2017 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት አመላካች አፈጻጸም እንዲሁም የሪፎርም እና አገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን እና የተማሪ ውጤትን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን ምዘናው በቢሮ ከሚገኙ ስራ ክፍሎች ጀምሮ በክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም በሁሉም የመንግስት 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ  ቢሮው በበጀት አመቱ በትምህርት ተቋማቱ ከምዘና ባሻገር ተደጋጋሚ ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው ምዘናው ተቋማቱን ወደ ተቀራረበ የአፈጻጸም ደረጃ በማምጣት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

ቢሮው በየደረጃው የሚያካሂደው የድጋፍና ክትትልም ሆነ የምዘና ስርአት የትምህርት ስራው ውጤታማ እንዲሆን እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ምዘናው የተካሄደባቸው የትምህርት ተቋም አመራሮች ገልጸው ምዘናው ተቋማቱ ያቀዱትን እቅድ ምንያህል ተግባራዊ እንዳደረጉ የሚረጋገጥበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኸኝ፣ከሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ እንዲሁም ከሪፎርም ባለሙያው አቶ አስናቀ ጋር በመሆን ምዘናው ከተካሄደባቸው ተቋማት መካከል በተወሰኑ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው ሂደቱን ተመልክተዋል።

ምዘናው በነገው እለትም ቀጥሎ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 128 ክላስተር ማዕከላት የሚካሄድ ሲሆን በቀጣይ የምዘናውን ውጤት መሰረት በማድረግ የተሻለ አፈጻጸም ለሚያስመዘገቡ ተቋማት ዕቅውና የሚሰጥ ይሆናል።

.

Copyright © All rights reserved.