በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያለውን የትምህርት መሠረተ ልማት እጥረት ለማቃለል እንዲሁም የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሻሻል ግንባታቸው በአጭር ጊዜ እና በጥራት የተጠናቀቁት እነዚህ ፕሮጀክቶች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሣው እና የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ እንድሁም የክፍለ ከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመረቁ፡፡
.