About ላለፉት ሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁ ተገለፀ።

ላለፉት ሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁ ተገለፀ።

14th June, 2025

ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለሞ ሙላቱ ገልፀዋል።

ሀላፊው በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ፈተናውን መውሰድ ካልቻሉ ጥቂት ተማሪዎች በስተቀር አብዛኞቹ ተማሪዎች መፈተናቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ፈተናው በጭር ጊዜ ውስጥ ታርም ይፋ ይደረጋል  ብለዋል።

አያይዘውም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የተመደቡ የጸጥታ አካላ ፣ ፈታኞች ፣ የጣቢያ ኃላፊዎች ፣ ሱፐርቫይዘሮችና የፈተና አስፈጻሚዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በትጋት በመወጣታቸው ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.