በክፍለ ከተማው አስተዳደር በወረዳ 9 የሚገኘው የጀነራል ታደሰ ብሩ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት G+2 የክፍል ማስፋፊያ ህንጻ እና በወረዳ 10 የሚገኘው ምዕራፍ ቁ.2 ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት የክፍለ ከተማው አስተዳደር የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በማቃለል ተጠቃሚነቱን ይበልጥ ለሚያረጋገጥ ለልማት ፕሮጀክቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን በክፍለ ከተማችን በመገንባት ላይ የሚገኙት የልማት ፕሮጀክቶች የዚሁ ጥረት አካል ናቸው ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም በተለይም በክፍለ ከተማው እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን የአገልግሎት ችግሮችን የሚቀርፉና የስራ ዕድል የሚጨምሩ በመሆናቸው ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ ብለዋል።
በዛሬው ዕለት ለምርቃት የበቁት ትምህርት ተቋማት አስተዳደሩ ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ናቸው ብለዋል ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ዕውን እንዲሆን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የትምህርት ዘርፉ አመራሮችና መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ የተማሪ ወላጆች ፣ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
.