Announcement የሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ተገመገመ።

የሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ተገመገመ።

09th August, 2025

በመርሀግብሩ የእቴጌ መነን የልጃገረዶች ፣ የገላን የወንዶች እና የብርሀን የአይነስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትን ጨምሮ የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የዛሬው መርሀግብር በሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ ሰርተው የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል መዘጋጀቱን ገልጸው የመርሀግብሩ ተሳታፊዎች በበጀት አመቱ የነበሩ ስኬቶችን አጠናክረው በማስቀጠል እና በሂደት የተስተዋሉ የአፈጻጸም እጥረቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በዕውቀታቸው እና ክህሎታቸው የላቁ እንዲሁም በስነምግባራቸው ምስጉን የሆኑ ተማሪዎችን በማፍራት ላይ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ጠቁመው ተቋማቱ በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር የማሻሻል ስራቸው በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመርሀግብሩ የሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት ትንተናን ጨምሮ በአመቱ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም መሪ እቅድን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።

.

Copyright © All rights reserved.