በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት "ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 20ኛውን የብሔር ብሔረሰብ ቀንን አስመልክቶ በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ።
መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ኬኔ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ወንድማማችነት እና እህትማማችነት የሚጎለብትበት ፤ መተሳሰብ እና አብሮነት የሚደምቅበት እንዲሁም ብሔር ብሔረሰቦች እሴቶቻቸውን እና ባህሎቻቸውን የሚያሳድጉበት በመሆኑ መጪው ትውልድን ይህንን በመረዳት ቀኑን በልዩ ሁኔታ ማክበር ይኖርበታል ብለዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ት ወይንሸት አስናቀ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጥንትም አብረው የኖሩ ፣ አሁንም ነገም አብረው የሚኖሩ የተጋመዱ ህዝቦች መሆናቸውን በጋራ ሠርተን በላቀ ትጋት የሠራናቸው የልማት ስራዎች ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
በመጨረሻም በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች ሰርተፍኬት ተበርክቷል።
.