Announcement የምስራቅ ጎህ የሳይንስ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት እንዲችል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡

የምስራቅ ጎህ የሳይንስ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት እንዲችል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡

09th October, 2026

የምስራቅ ጎህ የሳይንስ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት እንዲችል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡


(መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መአዛ መንግስቱ ጋር በመሆን በመሀል ካሳንችስ በሚገኘውና ዘንድሮ የልህቀት ማዕከል ሆኖ በአዲስ መልክ ስራ በጀመረው ምስራቅ ጎህ የሳይንስ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የመማር ማስተማር ስራውን በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ትምህርት ቤቱ በ2019 ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡና በሳይንስ ትምህርት ተሰጥኦ ያላቸዉን ተማሪዎች በመቀበል ዘንድሮ የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩን ጠቁመው ብቃታቸው የተረጋገጠ የትምህርት አመራሮችና መምህራን ተመድበው በስራ ላይ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡


ኃላፊው አያይዘውም በተቋሙ ስታንዳርዱን የጠበቀ የትምህርት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ግብዓት የማሙዋላትን ጨምሮ ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን ገልጸው የትምህርት ቤቱ በዚህ ልክ ስታንዳርዱን ጠብቆ የመማር ማስተማር ስራ እንዲጀምር መደረጉ ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠዉን ልዩ ትኩረት ከማሳየቱ ባሻገር ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መአዛ መንግስቱ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ ለሀገራችን ሁለተናዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ታስቦ ስራ እንደመጀመሩ የክፍለከተማው አስተዳደር ተቋሙ የቋቋመበት አላማ ግቡን እንዲመታ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.