(ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) አራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የዳግማዊ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከመደበኛው የመማር ማስተማር ስራ ባሻገር በከተማ ግብርና ስራ ውጤታማ በመሆን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በትምህርት ቤቱ ተግባራዊ የሆነው የከተማ ግብርና በዋናነት በመምህራን ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ጋዲሴ ደረሰ ገልጸው ፕሮግራሙ በትምህርት ቤቱ ተግባራዊ መደረጉ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር የማየት እድል እደፈጠረላቸው አመላክተዋል።