በልምድ ልውውጡ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የክፍለ ከተማው ተማሪ ወላጅ መምህር አባላት፣የትምህርት ቤት ወተመህ ሰብሳቢዎች እና የወረዳ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የትምህርት ተቋማት መካከል የወተመህ አደረጃጀትን በማስተባበር የትምህርት ቤቱን ምድረ ግቢ ምቹ ከማድረግ ጀምሮ የመማር የማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን ያከናወናቸው ተግባራት ለሌሎች ተሞክሮ ስለሚሆን የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስራዎች አስተባባሪ ወይዘሮ መአዛ ተስፉ ጠቁመው የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎችም በትምህርት ቤቱ ያገኙትን ተሞክሮ በየተቋማቸው ተግባራዊ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሰለሞን ዲሮ በበኩላቸው የትምህርት ቤቱ የወተመህ አባላት ከትምህርት ቤቱ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን በተቋሙ አከባቢ የነበሩ አዋኪ ተግባራትን ከማስወገድ ጀምሮ ከተለያዩ አካላት ከፍተኛ ገንዘብ በመሰብሰብ ምድረግቢውብ በቴራዞ እና ኮንክሪት የማስዋብ ስራ በመስራት እና የከተማ ግብርና ተግባርን በመደገፍ ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
.