በመርሐግብሩ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ ፣ በክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደመቀ ዋኘው፣ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም እንዲሁም ከሁሉም የክፍለ ከተማው ትምህርት ቤት የተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን በተገኙበት የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ማስጀመሪያ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጉብኝት አካሂደዋል ።
የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ እንዳሉት የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ተቋማትና በክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በሌማት ትሩፋት ዘርፍ ተግባር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሠራበት የሚገኝ ሲሆን፣ በአስኮ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ በሌማት ትሩፋት ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ስራ መስራቱን ጠቅሰው መምህራንም ከሚመረተው ውጤት በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት መቻላቸው በመማር ማስተማር ሥርዓቱ ላይ የተረጋጉ እንዲሆኑ እድል ይፈጥራል ሲሉ ገልጸዋል::
የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም በበኩላቸው የሌማት ትሩፋት ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተሠራበት የሚገኝ ቢሆንም ለሌሎች ትምህርት ቤቶችም አርአያ የሚሆነው አስኮ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባር ቀደም በመሆኑ ይህንን ልምድ የማስፋት ሥራ የሚሠራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።
.