Home በልደታ ክ/ከተማ የ2 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጂ+4 ማስፋፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

በልደታ ክ/ከተማ የ2 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጂ+4 ማስፋፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

03rd January, 2026

በክ/ከተማው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የፍሬህይወት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጂ+4 የማስፋፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በማስፋፊያ ግንባታው ማስጀመሪያ ወቅት እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባን ህፃናትን ለማሳደግ ምቹ ከተማ እናደርጋለን የሚለውን የክብርቲ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ኢንሼቲቭ ወስደን በትምህርቱ ዘርፍ በመተግበር እና ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት አበረታች ውጤት አስመዝግበናል ብለዋል።

የማስፋፊያ ግንባታው የትምህርት ተደራሽነትን፣ ጥራትን እና ደረጃን በማሻሻል የመማር ማስተማር ስራን ለማሳለጥ እየሰራነው ላለንው ተግባር አጋዥ ይሆናል ያሉት ዶ/ር ዘላለም ግንባታው በአጠረ ጊዜ ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባም ገልፀዋል።

በተጨማሪም ለትውልድና ለሀገር ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቶ ይህንን የማስፋፊያ ግንባታ ወደ ተግባር ላስገባው ለልደታ ክ/ከተማ አስተዳደርም በት/ቢሮ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ዛሬ ያስጀመርነው የማስፋፊያ ግንባታ  በመምህራን፣ በወላጆችና በተማሪዎች  ዘንድ ለረጅም ዓመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ የነበረ ነው ብለው አስተዳደሩም ይህንን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ ግንባታውን አስጀምሯል ሲሉ ገልፀዋል።

የማስፋፊያ ግንባታው የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል እየተሰሩ ላሉ ተግባራት ተደማሪ አቅም ይሆናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተቋማትን በአሰራር እና በአደረጃጀት እንዲዘምኑ በማድረግ በእውቀትና በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድን ለመፍጠር በትጋት እንሰራለን በማለት ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም መንግስት ከለውጡ በፊት በትምህርት ዘርፉ የነበሩ ስብራቶችን በመጠገን በእውቀት የዳበረ ተመራማሪ የሆነ ሀገርን የሚረከብ ትውልድ ለመገንባት እየሰራ ነው ብለው እንደ ልደታም ተግባሩን ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።


.

Copyright © All rights reserved.