Announcement በልደታ ክ/ከተማ የተገነቡ 2 ት/ቤቶችና 3 የህፃናት ማቆያዎች ተመረቁ፡፡

በልደታ ክ/ከተማ የተገነቡ 2 ት/ቤቶችና 3 የህፃናት ማቆያዎች ተመረቁ፡፡

25th May, 2026

በልደታ ክ/ከተማ ለትውልድ ግንባታ መሰረት የሚጥሉ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት ከለውጡ በፊት አብዛኞቹ ት/ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ ያልሆኑ ምቹ የተማሪዎች መቀመጫ ያለነበራቸው ነበሩ ብለው ትውልድ ተኮር ሰው ተኮር የሆነው የለውጡ መንግስት ሀገር የምትገነባው በትምህርት መሆኑን እምነት ይዞ ት/ቤቶች ላይ በመስራት መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ችሏል በማለት ተናግረዋል።
ከለውጡ ቀደም ብሎ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ሁሉም ህፃናት እድል የማያገኙበት ገንዘብ ያላቸው ብቻ የሚማሩበት ነበረ ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ መንግስት ይህንን አስተሳሰብ በመቀየር ሁሉም ህፃናት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የሚያገኙበትን ዕድል ፈጥሯል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጲያን በፅኑ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ላይ መስራት ያስፈልጋል ብለው በዚህም የለውጡ መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት በመስጠት ከዩኒቨርስቲ የሚስተካከሉ ት/ቤቶችን ከመገንባት ባለፈ የተማሪዎች የምገባ ስርዓት በመዘርጋትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የወላጆችን ሸክም እያቃለለ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ባደረጉት ንግግር የለውጡ መንግስት ሀገር የምትሰራው ትውልድ ሲሰራ ነው የሚል መርህን አንግቦ በትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት አድርጓል ብለው በዚህም ባለፍት የለውጥ ዓመታት ደረጃቸውን የጠበቁ ለመማር ማስተማሩ ምቹ የሆኑ ት/ቤቶችን በመገንባትና በግብዓት የማሟላት ተግባር በማከናወን ትውልድ ግንባታ ላይ በትኩረት ሰርቷል ሲሉ ገልፀዋል።ከለውጡ ወዲህ ደረጃቸውን የጠበቁ ምቹ፣ ሳቢና ማራኪ ት/ቤቶችን ከመገንባት ባለፈ ህፃናት ስለሚለብሱትና ስለሚበሉት እንዳይጨነቁ በግብዓትና በወላጅ ገቢ ማነስ ከትምህርታቸው ወደ ኃላ እንዳይቀሩ ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን የገለፁት የትምህርት ቢሮ ኃላፊው በዚህም የወላጆችን ሸክም ያቃለለ የምገባ ስርዓትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ በስነ-ምግባር የታነፀ እና ውጤታማ የሆነ ትውልድ የመገንባት ሂደቱን አጠናክሮ ቀጥሏል በማለት ገልፀዋል።የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደገለፁት የበጀት ዓመቱን ስንጀምር ከነዋሪዎቻችን ጋር ምክክር አድርገን ማህበረሰቡ ያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ነቅሰን በመያዝ ወደ ዕቅድ ቀይረን በተቀየረ 24/7 የስራ ባህል እቅዳችንን በመተግበር 70 ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለረጅም ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ የማህበረሰቡ ችግሮች ምላሽ እንዲያገኙ አስችለናል ብለዋል።

አስተዳደሩ ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ ትውልድን በስነ-ምግባር የሚያንፁ ፣ በአካልና በስነ-ልቦና የዳበረ እንዲሆን የሚስችሉ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በዚህም ት/ቤቶችን፣ የህፃናት ማቆያዎችን፣ የህፃናት መዋያዎችንና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል።በበጀት ዓመቱ የኑሮ ውድነትን የሚያቃልሉ ፣ትውልድን የሚቀርፁ፣ ለማህበረሰቡ ማህበራዊ እፎይታን የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን ገንብተን በማስመረቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ይህንን ስራ ስናከናውን ከጎናችን የነበራቹህ ባለሀብቶች እና ነዋሪዎች ምስጋና ይገባቹሃል ብለዋል።.

Copyright © All rights reserved.