(ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ እየተሰጠ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የመጨረሻ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና አሳጣጥ ሂደትን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ከቢሮ ማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን ምልከታ አድርገዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በ131 መፈተኛ ጣቢያዎች በበይነ መረብ እየተሰጠ የሚገኘው ፈተና የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከ2ሺ በላይ የፈተና አስፈጻሚዎች በየፈተና ጣቢያው ተመድበው ሂደቱን በመከታተል ላይ መሆናቸውን አስገንዝበው ፈተናው ያለምንም ችግር እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል:

.