Announcement የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ያላቸውን ቀሪ ጊዜ በመጠቀም ለፈተና ዝግጁ መሆን እንሚጠበቅባቸው ተገለፀ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ያላቸውን ቀሪ ጊዜ በመጠቀም ለፈተና ዝግጁ መሆን እንሚጠበቅባቸው ተገለፀ።

13th June, 2026

ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ስኬት ምቹ ምኅዳር ለመፍጠር የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልፃል።የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 24 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 17 ቀን የ2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅት ተከናውኗል ብለዋል።በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸው የተጠቀሰ ሲሆን አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ-መረብ ይወስዳሉ ተብላል።ለዚህም ተማሪዎች በቂ የኮምፒውተር ልምምድ የሚያደርጉበት አሰራር መዘርጋቱ የተመላከተ ሲሆን የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ውስንነት ባሉባቸው አካባቢዎች ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ተገልፆዋል።ሀገር አቀፍ ፈተናውን ለሚወስዱ አካል ጉዳተኞችም ምቹ የመፈተኛ ከባቢን ለመፍጠርም ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብላል።የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢንተርኔት እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተገልፃል።ተፈታኝ ተማሪዎች ያላቸውን ቀሪ ጊዜ በመጠቀም ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጋቸውን እንዲሁም የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተገልፃል።

.

Copyright © All rights reserved.