About በተመረጡ የመንግስትና የግል 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዝቅተኛ ክፍል ደረጃ የንባብ ክህሎት ምዘና ተካሄደ።

በተመረጡ የመንግስትና የግል 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዝቅተኛ ክፍል ደረጃ የንባብ ክህሎት ምዘና ተካሄደ።

05th April, 2025

በተመረጡ የመንግስትና የግል 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዝቅተኛ ክፍል ደረጃ የንባብ ክህሎት ምዘና ተካሄደ።

(መጋቢት 26/2017 ዓ.ም) ምዘናው የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎችን የአማርኛ፣የአፋን ኦሮሞ እና የእንግሊዘኛ ቋንቋ የንባብ ክህሎት ያለበትን ደረጃ በመለየት በቀጣይ ድጋፍ የሚፈልጉ ተማሪዎችን በመደገፍ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ታስቦ መካሄዱን ከቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምዘናው ሰባት የመመዘኛ መሳሪያዎችን መሰረት አድርጎ መካሄዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመማር ብቃት ምዘና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብሩክ መንግስቱ ገልጸው በቀጣይ የምዘናው ውጤት በባለሙያዎች ተተንትኖ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት እንደሚደረግ  የምዘና ሂደቱን ለመከታተል በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች በተገኙበት ወቅት አስታውቀዋል።

ባለሙያው አያይዘውም ምዘናው ውጤታማ እንዲሆን ቀደም ሲል መዛኝ መምህራንን ጨምሮ ሂደቱን ለሚከታተሉና ለሚያስተባብሩ የፈተና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና መምህራን ምዘናው ስኬታማ እንዲሆን ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.