About በነገው እለት በተመረጡ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚካሄደውን የዝቅተኛ ክፍል ደረጃ የንባብ ክህሎት ምዘና ለሚከታተሉ ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።

በነገው እለት በተመረጡ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚካሄደውን የዝቅተኛ ክፍል ደረጃ የንባብ ክህሎት ምዘና ለሚከታተሉ ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።

05th April, 2025

በነገው እለት በተመረጡ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚካሄደውን የዝቅተኛ ክፍል ደረጃ የንባብ ክህሎት ምዘና ለሚከታተሉ ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።

(መጋቢት 25/2017 ዓ.ም) ኦረንቴሽኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የመማር ብቃት ምዘና ከፍተኛ ባለሙያዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ከመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በጋራ መስጠታቸውን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመማር ብቃት ምዘና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብሩክ መንግስቱ ኦረንቴሽኑ በነገው እለት ከሁሉም ክፍለ ከተሞች በተመረጡ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎችን የአማርኛ፣አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋ የንባብ ክህሎት መሰረት አድርጎ ለሚካሄደው ምዘና የተዘጋጀውን ፈተና በምን መልኩ ማስተዳደር እንደሚገባቸው እና የምዘናው ውጤት እንዴት እንደሚያዝ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መሰጠቱን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ በበኩላቸው ቀደም ሲል የዝቅተኛ ክፍል ደረጃ የንባብ ክህሎት ምዘናውን ለሚያካሂዱ መዛኝ መምህራን ከምዘና ሂደቱ ጋር በተገናኘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመው  የምዘና ሂደቱን ለሚደግፉ የክፍለ ከተማ የፈተና ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ከምዘና ሂደቱ ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ፈጥረው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ የዛሬው ኦረንቴሽን መሰጠቱን አመላክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.