Announcement የከተማ አቀፉ የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር

የከተማ አቀፉ የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር

28th June, 2024

የከተማ አቀፉ የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር የመዝጊያ መርሀ ግብር ተካሄደ።

(ሰኔ 20/2016 ዓ.ም) ስፖርታዊ  ውድድሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አዘጋጅነት ሲካሄድ ቆይቶ  በአዲስ ከተማ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መካከል በተደረገ የወንዶች እግር ኳስ የዋንጫ ጫወታ ፍጻሜውን አግኝቷል። ውድድሩ  በሁለቱም ጾታዎች በመረብ ኳስ እና ጠረጴዛ ቴኒስ እንዲሁም በወንዶች እግር ኳስ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በመረብ ኳስ ወንዶች አዲስ ከተማ በሴቶች ለሚኩራ በጠረጴዛ ቴኒስ ወንዶች ጉለሌ በሴቶች ቂርቆስ ሲያሸንፉ  አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ክፍለ ከተማ በወንዶች እግር ኳስ አዲስ ከተማን 2ለ1 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። በመምህራን መሀከል የሚካሄድ ስፖርታዊ ውድድር የእርስ በእርስ ግንኙነትን በማጠናከር ጤናማ የፉክክር መንፈስ የሚፈጥር ውድድር እንደመሆኑ ስፖርታዊ ውድድሩ ቀጣይነት ኖሮት በተጠናከረ መልኩ እንዲካሄድ ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በውድድሩ የማጠቃለያ መርሀ ግብር አስታውቀዋል። በመዝጊያ መርሀ ግብሩ በሶስቱ የስፖርት አይነቶች እና በአጠቃላይ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ክፍለ ከተሞች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል፣ከወጣቶችና ስፖርት ቢሮ  ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዳዊት ይፍሩ እና ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ከአቶ ድንቃለም ቶሎሳ የዋንጫ ሽልማት ተቀብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! 

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com     

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

.

Copyright © All rights reserved.